Welcome




Plan your Summer Trip at ESCFE festival to GENEVA!

17 – 20 JULY 2013 AT GENEVA, SWITZERLAND

Don’t miss this extra ordinary event. A Remarkable Occasion to taste the feeling of Ethiopia. More from Ethioswiss.com website.





አዘጋጅዋ ሀገር የ2012 ዋንጫ በቤቷ አስገባች [PDF]

የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በህግና ደንብ ተደራጅቶ የዛሬ 10 ዓመት በስቱትጋርት ጀርመን ላይ ውድድር ማካሄዱ ይታወቃል፤ እነሆ የዘንድሮን አመት እንዲያዘጋጅ የተፈቀደለት የኢትዮ ጣሊያን የስፖርት ቡድን ከአሁን ቀደም ተደርጎ ከነበሩት ዝግጅቶች በእጅጉ የተሻለ እንደነበረ ታይቷል፤ ከአሁን በፊት በአምስተርዳምና በኑረንበርግ ለሶስት ቀን ተደርጎ የነበረውን የስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮ ጣሊያን ስ ፖርት ክለብ ወደ አራት ቀን ከፍ እንዲል አድርገውታል፤ ኢትዮጵያው ያን ከአውሮፓ ከአሜሪካ ከኢትዮጵያና ከተለያየ አካባቢ ከአንድ ሳምንት በፊት ወደ ጣሊያን ሮማ ከተማ በመግባት ከተማዋን ሲያጨናንቁዋት ታይቷል፤ ይህ የአየሩ ከፍተኛ ሙቀት ያልበገረው የስፖርት ታዳሚ ሳምንቱን ሙሉ ቀን ቀን በእግር ኳስ ማታ ማታ በኮንሰርት ጭፈራዎች ብዛት ባላቸው ዲጄዎችና ድምጻውያን ሲዝናኑ ከርመዋል፤ በተለይ ከአሁን በፊት ለአስር አመታት የታዩትን የአልቢትሮዎች ችግር በጣሊያን ሀገር የተቀረፈ ይመስላል ቁጥራቸው ወደ 28 የሚጠጉ ዳኞች ከቡድን መሪያቸው ጋር በመሆን ወደሜዳው ሲመጡ ተጋጣሚ ቡድን ይመስሉ ነበር፤

የኢትዮ ጣሊያን የበአል አዘጋጅ ኮሚቴዎችም ከጠበቅነው በላይ አልቢትሮዎች ስለመጡብን ይቅርታ ይደረግልን በማለት ከፌዴሬሽን ተመራጮች ጋር ሲቀልዱ ታይቷል ፤ ይህ ሁኔታ ወደፊትም ከተደገመ በአጫዋቾች የነበረብን ችግር ተወገደ ማለት ሲሆን ወደ ሚቀጥሉት እንደቴሴራ ኮንትሮል ወደመሳሰሉት ስራ ይገባል ተብሎ ይታመናል ፤የዘንድሮው ውድድር እንደ ሁልግዜው በዲሲፕሊን ያለምንም ረብሻ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በሰላም ተጠናቋል ፤የመጨረሻው የዋንጫ ጨዋታ ቅዳሜ ጁላይ 28 ቀን 2012 ከሰዓት በሗላ ብዙ ህዝብ በተገኘበት ተፈጽሟል፤

www.escfe.org የዌብሳይት ሰንጠረዣችን እንደሚያስረዳው ወድድሩ በሶስት ምድብ ተከፍሎ የተከናወነ ሲሆን ከምድብ ሶስት በጥሩ ሶስተኝነት አራት ውስ ጥ በመግባትና ለዋንጫ ሽሚያ የደረሰው ያዘጋጅዋ ሀገር የኢትዮ ጣሊያን ሰፖርት ቡ ድን ሲሆን ከሌላ በኩል ከምድብ አንድ ተጋጣሚዎቹን እያሸነፈ ሩብና ግማሽ ፍጻሜን አልፎ የመጣውን የስቱትጋርት ክለብ ጋር የፍጻሜውን ጨዋታ በማድረግ ባጋጠማቸ ው ፍጸም ቅጣት ምት አንድ ጎል በማግባታቸውና በዚሁ የጎል ብልጫ በመጠናቀቁ ኢትዮ ጣሊያን የዘንድሮው የ2012 ዋንጫ ባለቤት ሆነዋል ፤

በሌላ በኩል የተሳታፊ ቡድኖች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ በዘንድሮ ውድድር 2012

8 ቡድኖችን ወደ 2ተኛ ዲቪዚዮን ተከፍለው የተጫወቱ ሲሆን በውጤቱም የለንደን ካታንጋ ቡድን ተጋጣሚውን የናይል ኤፍሴ ለንደንን ቡድን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል እንኝህ ሁለት ቡድኖች ለቀጣዩ ዓመት ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን መውጣታቸውን አረጋግጠዋል ፤ በሌላ በኩል ለዚሁ በዓል ለመዝናናት ከአውሮፓ የመጡ ህጻናት በጣሊያን ሀገር ከሚኖሩ ህጻናት ጋር የእግር ኳስ ግጥሚያ ተካሄዶ በአውሮፓ ህጻናት ቲም አሸናፊነት ተጠናቋል፤ እንኝህ ተስፋ የሚጣልባቸው ህጻናት ድንቅ ችሎታቸውን ለተመልካች አሳይተዋል ፤እንዲሁም በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ ያለፈውን ወንድማችን ሚ ኪን ለማስታወስ በፌዴሬሽኑ የስራ አመራርና በሚኪ የቅርብ ጓደኞች መሃል በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ፌዴሬሽኑ የበላይነትን በማሳየት አሸንፎ የሚኪን ዋ ንጫ ለስቱትጋርት ክለብ ተሰጥቷል፤ እንዲሁም በአውሮፓ የሚገኙ የቀድሞ እግር ዃስ ተጫዋቾች ማህበር በጣሊያን ሀገር ከሚገኝ አንድ ክለብ ጋር ግጥሚያ ማካሄዱ ታይቷል፤

ከሜዳው አካባቢ ያልተለዩት የቀይ መስቀልና የፌዴሬሽን ስራ አመራሮች፤